በኢራቅ የተስፋፋዉ ካንሰር11 ጥቅምት 2002ረቡዕ፣ ጥቅምት 11 2002በኢራቅ በተከታታይ የተካሄዱ ጦርነቶች የማይሽር ጠባሳ እንደጣሉ ይፋ የወጡ መረጃዎች እየጠቆሙ ነዉ።https://p.dw.com/p/KCaNተዋህሲዉ በአጉሊ መነፅር ሲታይማስታወቂያ ከቀደምት የስልጣኔ ምንጭነት ባሻገር በነዳጅና ጋዝ ክምችቷ ተጠቃሽ በሆነችዉ ኢራቅ ለዓመታት በተካሄደባት ጦርነት ለጥቃት የዋሉ ዩራኒየም የተሰኘዉን ንጥረነገር የያዙ አረሮች በርካቶችን ለሳንባ ነቀርሳ ዳርገዋል። ወትሮ ይታወቅ የነበረዉ ቁጥርም ከእጥፍ በላይ ጨምሯል። ህፃናትም አካላቸዉ ጎድሎ እንዲወለዱ ምክንያት ሆኗል። ነብዩ ሲራክ ሸዋዬ ለገሠ