በአፍሪቃ ቀንድ ረሃብና ድርቅን መቋቋሚያ ስልት
ረቡዕ፣ ሰኔ 22 2008ማስታወቂያ
በአፍሪቃ ቀንድ ረሃብ እና ድርቅን በዘላቂነት መቋቋም የሚያስችል ስልት መቀየስ በሚቻልበት መንገድ ላይ የመከረ ስብሰባ አዲስ አበባ ውስጥ ተካሄደ ። የአፍሪቃ ህብረት ባዘጋጀው በዚሁ ስብሰባ ላይ የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት በምህፃሩ ኢጋድ አባል ሃገራት ተወካዮች እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ተጠሪዎች ተገኝተዋል። ተሳታፊዎቹ ባለፈው ዓመት የአፍሪቃ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ችግሩን ለመከላከል ያስችላሉ ሲል ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ተግባራዊ የሚሆኑበትን መንገድ ይቀርፃሉ ። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ