በአፋር ክልል የተነሳው ግጭት
ሰኞ፣ ሚያዝያ 13 2006ማስታወቂያ
በአፋር ክልል በአኒባራ ወረዳ ባለፈው ቅዳሜ በ 2 ጎሳዎች መካከል በተፈጠረ ግጥት 8 ሰዎች ሞተዋል ሲሉ ዓይን ምስክሮች ተናገሩ ። ከግጭቱ በኋላም በአዋሽና በሌሎች አካባቢች ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ወደ ከኢትዮጵያ ወደ ጅቡቲ ከጅቡቲም ወደ ኢትዮጵያ የሚወስደው መንገድ ተዘግቶ እንደነበርም ነዋሪዎች ለዶቼቬለ ተናግረዋል ።የኢትዮጵያ ፌደራል ጉዳዮች መስሪያ ቤት በበኩሉ ሰዎች መሞታቸውን የሚያመለክት መረጃ እንዳልደረሰው አስታውቋል ። መስሪያ ቤቱ በአካባቢው የሚፈጠሩ ግጭቶችን በዘላቂነት ለመፍታት የተለያዩ ሥራዎችን በማከናውን ላይ መሆኑንን ገልጿል ። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሀንስ ገብረ እግዚአብሄር ዝርዝር ዘገባ አለው ።
ዮሀንስ ገብረ እግዚአብሄር
ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ