በአዲስ አበባ የኦሮምያ ልዩ ጥቅሞችን የተመለከተ ረቂቅ አዋጅ
ማክሰኞ፣ ሰኔ 20 2009ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኦሮምያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖረውን ልዩ ጥቅምን በተመለከተ የተሰናዳውን ረቂቅ አዋጅ ዛሬ ለኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስተላለፈ። የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን እንደዘገቡት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ረቂቅ አዋጁ በኢትዮጵያ ህገ መንግሥት አንቀፅ 49 ንኡስ አንቀጽ 5 የተቀመጡትን ከአገልግሎት አቅርቦት ከተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም እና ከአካባቢ ጥበቃ ጋር የተያያዙ ልዩ ጥቅሞች ያላቸውን ማካተቱን አስታውቋል። በረቂቅ ህጉ አዲስ አበባ እና ኦሮምያን ያስተሳስራሉ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን ማዕከል በማድረግ የኦሮምያ ክልልን ልዩ ጥቅም ለማስጠበቅ ያስችላሉ የተባሉ አንቀጾች መካተታቸውም ተዘግቧል። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ስለ ረቂቅ አዋጁ ምንነት ባጭሩ ገልጿል።
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሔር
አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ