በአውሮፓ የኦሮሞ ተወላጆች ሰልፍ በብራሰልስ
ዓርብ፣ ሰኔ 13 2006ማስታወቂያ
ባሳዩበት ወቅት ፣ ፖሊስ በወሰደው ርምጃ ፣ ተማሪዎች መገደላቸውን መቁሰላቸውንና ተይዘው መታሠራቸውን በመቃወም ፤ በጀርመን ሀገር የሚኖሩ የብሔሩ ተወላጆች በቅርቡ በርሊን ውስጥ አደባባይ በመውጣት የተቃውሞ ሰልፍ ማሳየታቸውን ከዚህ ቀደም መዘገባችን የሚታውስ ነው ። በዛሬው ዕለትም የአውሮፓው ሕብረትና የአውሮፓ ፓርላማ ፣ እንዲሂም የኔቶ መቀመጫ በሆነችው የቤልጅግ መዲና ብራሰልስ ከተለያዩ የአውሮፓ ሃገራት በመሰባሰብ ዛሬ እኩለ ቀን ገደማ ላይ ተመሳሳይ ሰልፍ ማሳየታቸው ታውቋል። ሰ።ልፉ በተካሄደበት ሥፍራ ተገኝቶ የነበረው የብራሰልሱ ዘጋቢአችን ገበያው ንጉሤ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
ገበያው ንጉሤ
ተክሌ የኋላ
ኂሩት መለሰ