በአባይ ተፋሰስ ላይ የተካሄደ ዐውደ ጥናት
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 23 2006ማስታወቂያ
ስለ አባይ ወንዝ አጠቃቀምና ስለ ህዳሴው ግድብ በእውቀት ላይ የተመሰረተ መረጃ የሚቀርብበት ስ
ርዓት መዘርጋቱ ተገለጠ ። የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ባይሌ ዳምጤ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ስር በተቋቋመው ብሉ ናይል በተባለው ተቋም አማካይነት በአባይ ላይ የተሰሩ ምርምሮችን በማሰባሰብ ተማራማሪዎችና ፖሊሲ አውጭዎችና መረጃውን የሚፈልጉ የተለያዩ አካላት እንዲያገኙት ለማስቀመጥ ተሞክሯል ። ተቋሙ በአባይ ውሃ ላይ ተጨማሪ ጥናትና ምርምሮችን በማድረግ በመስኩ ያለውን እውቀት ለማሳደግ በመጣር ላይ መሆኑንም አስታውቀዋል ። ባህር ዳር ዩኒቨርስቲ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን በአባይ የውሃ ሃብት ፍትሃዊ አጠቃቀም ላይ በተወያዩበት የሁለት ቀናት ስበሳባ ላይ ዶክተር ባይሌንና ሌሎች ተሳታፊዎችን ያነጋገረው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኅይለ ጊዪርጊስ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል ።
ጌታቸው ተድላ ኅይለ ጊዪርጊስ
ሂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ