በአማራ ክልል ከሞላ ጎደል መረጋጋት እየታየ ነዉ
ማክሰኞ፣ ሰኔ 18 2011ማስታወቂያ
በተለይ ግድያው በተፈፀመባት በባሕርዳር ከተማ የታጠቁ የፀጥታ ኃይሎች በየቦታዉ በርከት ብለዉ እንደሚታዩ ተገልጿል። በጀነራል አሳምነዉ ፅጌ የትውልድ ከተማ ላሊበላም ተመሳሳይ ውጥረት ሰፍኖ የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ስዓት ግን መረጋጋት መታየቱን የአካባቢዉ ባለስልጣናት መግለፃቸው ተሰምቷል። ዝርዝር ዘገባውን የባሕር ዳሩ ወኪላችን ዓለምነው መኮንን በስልክ አስተላልፎልናል።
ዓለምነው መኮንን
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ