በናይጀሪያ የቀጠለው ውዝግብ22 ጥር 2002ቅዳሜ፣ ጥር 22 2002በአፍሪቃ በህዝብ ብዛት ቀዳሚውን ቦታ የያዘችው ናይጀሪያ በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ ትገኛለች።https://p.dw.com/p/LnW4የናይጀርያዉ ምክትል ፕሪዝደንት ጆናታን ጉድላክምስል APማስታወቂያየሀገሪቱ ፕሬዚደንት ኡማሩ ያር አዱዋ ለህክምና ከብዙ ጊዜ ወዲህ በውጭ ሀገር በሚገኙበት ባሁኑ ጊዜ በጆስ ከተማ በክርስትያኖችና በሙስሊሞች መካከል በተፈጥሮ ሀብት ክፍፍል እና በንብረት ባለቤትነት ጥያቄ ግጭት መፈጠሩ የናይጀሪያ መንግስት የሚገኝበትን የቀውስ ሁኔታ እያካረረው ተገኝቷል። በውዝግቡ እንደሚታወሰው ከሶስት መቶ የሚበልጥ ሰው ተገድሎዋል። አርያም ተክሌ DPA/DW