በተለያዩ የዩናይትድ ስቴትስ ከተሞች የቀጠለዉ ተቃዉሞ
ሰኞ፣ ኅዳር 29 2007ማስታወቂያ
የዩኤስ አሜሪካ የፀጥታ አስከባሪ ፖሊስ ፈርገሰንና ኒዮርክ ከተማ ዉስጥ ያልታጠቁ ጥቁሮችን መግደሉ ይታወቃል። በዩኤስ አሜሪካ ኦባማ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ፤ 53 % ነዋሪዎች በጥቁር እና በነጭ አሜሪካዉያን ዘንድ ያለዉ የዘር ጥላቻ ሻክሮአል ሲሉ እንደሚያምኑ፤ 46 % ጥቁር አሜሪካዉያንም ይኸዉ አይነት እምነት እንዳላቸዉ ይገልፃሉ። 36 % የአሜሪካ ነዋሪ ደግሞ በኦባማ አስተዳደር ምንም አይነት ለዉጥ እንዳልታየ ይህ ሁኔታ በፊትም እንደነበር መግለፃቸዉን የወጣዉ ዝርዝር ያመለክታል። በዩናይትድ ስቴትስ የቀጠለዉን ተቃዉሞ በተመለከተ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘዉን ወኪላችንን ስቱድዮ ስለ ተቃዉሞ ጠይቀነዉ ነበር።
መክብብ ሸዋ
አዜብ ታደሰ
አርያም አብርሃ