በቩርስቡርግ የባቡር ጥቃት
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 12 2008ማስታወቂያ
ከአፍጋኒስታን የመጣ ተገን ጠያቂ ነው የተባለው አጥቂ በፖሊሶች መገደሉን የባቫሪያ ሀገር አስተዳደር ሚንስቴር ባለስልጣናት አስታውቀዋል። ጥቃቱ ከሽብርተኝነት ጋር የተያያዘ መሆን አለመሆኑ በወቅቱ ምርመራ በማካሄድ ላይ እንደሚገኝ ያካባቢው ፀጥታ ባለስልጣናት ገልጸዋል። ባቡር ውስጥ ስለተጣለው ጥቃት፣ ስለ አጥቂው እና ስለምርመራው በርሊን የሚገኘውን ወኪላችንን ይልማ ኃይለ ሚካኤልን ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬው ነበር። በመጀመሪያም የጠየቅሁት የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ሰዎች አሁን በምን ዓይነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ነው።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
አርያም ተክሌ
ሸዋዬ ለገሠ