በባህር የስደተኞች ሞት እና የመብት ተሟጋቾች ጥያቄ
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 13 2008ማስታወቂያ
አምናም ተመሳሳይ አደጋ ደርሶ በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ስደተኞች በሞቱበት ጊዜ፣ የአውሮጳ ህብረት ይህን መሳይ አሳዛኝ አደጋ እንዳይከሰት ለማከላከል እና ወደ አህጉሩ በሕገ ወጥ የሚገቡትን ስደተኞችንም ቁጥር ለመቀነስ በሰው አሸጋጋሪዎች አንፃር ቁጥጥሩን የማጠናከር ርምጃ መውሰዱ ይታወቃል፣ ያም ቢሆን ግን ስደተኞቹ አሁንም በማያስተማምኑ ጀልባዎች በሚያደርጉት ጉዞ ሕይወታቸውን ለአደጋ እያጋለጡ ነው። ይህ እንዳይሆን ታድያ ስደተኞች ወደ አውሮጳ በሕጋዊ መንገድ እንዲገቡ ህብረቱ ትክክለኛውን መስመር እንዲከፍትላቸው የመብት ተሟጋቾች መጠየቃቸውን ቀጥለዋል።
ገበያው ንጉሤ
አርያም ተክሌ
ነጋሽ መሀመድ