በሶርያና በእስራኤል የወደፊት ግንኙነት ላይ ያተኮረ ጉባዔ በደማስቆ29 ነሐሴ 2000ሐሙስ፣ ነሐሴ 29 2000የሶርያ፦ የፈረንሳይ፡ የቱርክና የቓታር መሪዎች ፤ ፕሬዚደንት በሺር አል አሳድ፤ ፕሬዚደንት ኒኮላ ሳርኮዚ፤ ጠቅላይ ሚንስትር ረቸፕ ጠይብ ኤርዶኻንና አሚር ሼኽ ሀማድ ቢን ኻሊፋ አል ጣኒ ዛሬ በሶርያ መዲና ደማስቆ ያካሄዱት ጉባዔ የቆየው አንድ ሰዓት ብቻ ቢሆንም፡ ጉባዔው ለሶርያ ትልቅ ትርጓሜ ይዞዋል።https://p.dw.com/p/FBY0ፕሬዚደንት አሳድና የፈረንሳዩ አቻቸው ሳርኮዚምስል APማስታወቂያምክንያቱም፡ እስከአሁን ከሞላ ጎደል የተገለለችው ሶርያ ለመካከለኛው ምስራቅ ሰላም በሚወርድበተ ጥረት ላይ ከፍተኛ ሚና ከያዙ የተለያዩ ሀገሮች ጋር በአንድ ጠረጴዛ ዙርያ እንድትቀመጥ አስችሎዋታል። የዚሁ ጉባዔ የሩቅ ዓላማ በሶርያና በእስራኤል መካከል መቀራረብ ሊኖር የሚችልበትን ዘዴ ማፈላለግ ነበር።