በሶሪያ ላይ የአሜሪካ ዛቻና ሩሲያ
ሰኞ፣ ጳጉሜን 4 2005
ያ ወዳጅ ሩስያም ዩኤስ አሜዪካ በሶርያ ላይ ጦርነት ከማንሳት ይልቅ ለሰላም ስምምነቱ ጥረት ብታደርግ ይሻላል ስትል ዛሪ አስታዉቃለች። የዩኤስ ኤዉ ዉጭ ጉዳይ ሚንስትር ጆን ኬሪ በበኩላቸዉ ሶርያ ያላትን የኬሚካል መሳርያ በሳምንት ግዜ ዉስጥ ካስረከበች የአየር ጥቃቱ እንደሚነሳ ተናግረዋል።
የሩስያዉ የዉጭ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ዩናይትድ ስቴትስ በሶርያ ላይ ጦር ከማንሳት ይልቅ የሰላም ድርድር ጥረት ብታደርግ ይሻላል በሚለዉ ሃሳብ ላይ ሀገራቸዉ ከሶርያ ጋር መስማማቷን ገልጸዋል። እንደ ሰርጌ ላቭሮቭ አሜሪካ በሶርያ ላይ ያቀደችዉ የአየር ጥቃት ሽብርተኛነት እንዲስፋፋ ምክንያት ይሆናል። በሌላ በኩል የሶርያዉ ፕሬዚዳንት ባሽር አልአሳድ የያዙትን የኬሚካዊ መሳርያ በአንድ ሳምንት ካስረከቡ ሶርያ ከተዛተባት የአየር ድብደባ ትድናለች ሲሉ የዩናይትድ ስቴትሱ የዉጭ ጉዳይ ሚንስትር ጆን ኬሪ ዛሪ ተናግረዋል። ኬሪ ሀገራቸዉ ሶርያ ላይ የአየር ጥቃት ለማድረግ የወሰነችዉ የሶርያዉ ፕሬዚዳንት ባሽር አልአሳድ ዳግም መርዘኛ ጋዝን ጥቅም ላይ እንዳያዉሉ ለማስቆም ነዉ ሲሉ ትናንት ፓሪስ ላይ መናገራቸዉ ይታወቃል። ኬሪ ዩናይትድ ስቴትስ በአሳድ መንግስት ላይ ላቀደችዉ የአየር ድብደባ ድጋፍ ለማሰባሰብ በፓሪስ በተደረገዉ የአረብ ሀገራት ማህበር ተወካዮች ስብሰባ ላይ እንደገለጹት፤ ሀገራቸዉ ከሌሎች ሃገራት በጋራ ስለ ሶርያ ጉዳይ መፍትሄ ለማግኘት በመጣር ላይ ናት።
« በሶርያ ጣልቃ ለመግባት ከአንደኛዉ ቡድን ለመወገን ወይም የሶርያዉን የእርስ በርስ ጦርነት የራስዋ ጉዳይ አድርጋ ለመረከብ አይደለም»
የዉጭ ጉዳይ ሚንስትር ጆን ኬሪ በሶርያ ላይ ወታደራዊ ጥቃት እንዲደረግ በሚለዉ አቋም ከአስር የማያንሱ የአሜሪካንን አቋም የሚከተሉ ደጋፊዎች እንዳላት ትናንት ፓሪስ ላይ መናገራቸዉ ይታወቃል። ዛሪ ለስድስት የቴሌዥን ጣንያ ቃለ ምልስ እንደሚሰጡ የተነገረዉ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በሶርያ ላይ ይደረግ ያሉትን ወታደራዊ ቅጣት ለማካሄድ አሜሪካዉያን እና የኮንግረስ አባላትን ለማሳመን የተቻላቸዉን ሁሉ እንደሚያደርጉ ነዉ የገለፁት።
በሌላ በኩል የሶርያ ወዳጅ የሆነችዉ ሩስያ ዩናይትድ ስቴትስ በሶርያ ላይ ጥቃት እንዳትጥል እየታገለች ትገኛለች። የሶርያ ፕሬዚዳንት ባሽር አልአሳድ ጅምላ ጨራሽ መሳርያን እንዳልተጠቀሙ በተደጋጋሚ መግለፃቸዉ ይታወቃል። የሩስያዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭና የሶርያዉ አቻቸዉ አል ሞአላም፤ ዛሪ ሞስኮ ላይ ተገናኝተዉ የተመድ የኬሚካል መሳርያ መርማሪ ቡድን ሶርያ ዉስጥ ዳግም ተመልሶ እንዲያጣራ ግፊት በማድረግ ዩናይትድ ስቴትስ በሶርያ ላይ የሰነዘረችዉን እጇን እንዳታነሳ አስጠንቅቀዋል። የሩስያዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ላቭሮቭ ከጦርነቱ ይልቅ ለሰላም ዉይይት ለመድረስ ጥረት ማድረግ ይገባል ይላሉ፤
« የሶርያ ተቃዋሚ ወገን መሪዎች ባለፈዉ ዓመት ሰኔ 23 ጄኔቭ ስምምነት የተደረሰበትን የመፍትሄ ሃሳብ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረግ ይቻል ዘንድ የሰላሙን ጉባዔ ያላንዳች ቅድመ ግዴታ የሚደግፉ ስለመሆናቸዉ ግልጽና የማያዳግም ፈቃደኝነታቸዉን ያረጋግጡ ዘንድ ከመጠየቅ አንቦዝንም»
አሜሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተደነገገን ቀይ መስመር የሶርያ መንግስት መጣሱን የምትከሰዉ፤ ሶርያ ዉስጥ ነሃሴ ወር አጋማሽ የተቃዋሚ ደጋፊዎች በሚገኙባቸዉ ከደማስቆ ወጣ ባለ አካባቢ በተተኮሰ ጅምላ ጨራሽ መሳርያ 426 ህፃናትን ጨምሮ ከአንድ ሽህ በላይ ሰዎች መገደላቸዉን ተከትሎ መሆኑ ይታወቃል።
አሁን በደረሰን ዘገባ መሰረት ደግሞ ሩስያ፤ ሶርያ ያላትን የኬሚካል ጦር መሳርያ በዓለማቀፉ ማሕበረሰብ ቁጥጥር ስር በማድረግ ከዩናይትድ ስቴትስ የአየር ድብደባና ዉድመት እንድትድን ጠይቃለች። ይህን የገለፁት የሩስያዉ የዉጭ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ናቸዉ።
አዜብ ታደሰ
ተክሌ የኋላ