ዋና መቀመጫዉን በእንግሊዝ ለንደን ያደረገዉ የአለም አቀፉ የባህር ትራንስፖርት አገልግሎት ቢሮ፣ በባህር ንግድ እንቅስቃሴ ወቅት የሚፈጸሙ ወንጀሎችን የሚቆጣጠረዉ ቢሮ በባህር ወደ ሶማልያ በሚገቡት የሰባዊ እርዳታ ቁሳቁሶች በወንበዴዎች እየተዘረፉ ነዉ ሲል ዛሪ ለዶቸ-ቬለ አስታዉቋል። በዚህ ጉዳይ ዙርያ አዜብ ታደሰ መቀመጫዉን ለንደን ያደረገዉን የአለም አቀፉን የባህር ትራንስፖርት ቢሮን አነጋግራለች