በሶማልያ በመባባስ ላይ ያለዉ የቦንብ ጥቃት
ሰኞ፣ ግንቦት 27 1999ማስታወቂያ
የአገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስትር አሊ መሃመድ ጊዲ፣ ትናንት፣ ለሶስተኛ ግዜ ከተጠነሰሰባቸዉ ጥቃት አምልጠዋል። ነገር ግን ሰባት ያህል የሚኒስትሩ ጠባቂዎቻቸዉ ተገድለዋል፣ በርካቶችም ቆስለዋል። በተያያዘ ዜና በትናንትናዉ እለት በመቅዲሾ ዉስጥ መንገድ ዳር የተጠመደ ቦንብ ያስከተለዉ ፍንዳታ፣ በኢትዮጽያ የጦር ሰራዊት ተሽከርካሪ ላይ ጉዳት አድርሶአል። ስለ ሶማልያ ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ጋዜጠኛ አዊስ ኦስማን ዩሱፍን፣ አዜብ ታደሰ በስልክ አነጋግረዋለች።