በስኬትቦርድ ከአዲስ አበባ እስከ ሀረር ጉዞ
ዓርብ፣ ሚያዝያ 18 2005ትንሽ ነው ከጠፍጣፋ እንጨት የተሰራ፣አራት ጎማዎች ያሉት ምናልባትም መካከለኛ መክተፊያ ያክላል። ሰሞኑን ፤ አዲስ አበባን ከሀረር ከሚያገናኘው ጎዳና ላይ እንደዚህ አይነት እንጨት ላይ ቆመው ወይንም በአንድ እግራቸው እየገፉና ጣውላው ላይ ዘለው እየቆሙ የሚጓዙ ወጣቶች አይታችሁ ከሆነ ፤ የስኬትቦርድ ነጂዎች ናቸው። ካሳለፍነው ማክሰኞ ጀምረው ከአዲስ አበባ -ሀረር ጉዞ ጀምረዋል። ትናንት አዋሽ ደርሰው ዕረፍት ሲያደርጉ ከጉዞ ተካፋዮቹ መካከል ሁለቱን በስልክ አነጋግረናቸዋል።
የ 16 አመቱ አቤነዘር ከሁለት አመት በፊት ነው እስኬትቦርድ መንዳት የተማረው። ዛሬ የዚህ ጉዞ ተካፋይ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ስኬትቦርድ የምንነዳ ከሰላሳ በላይ እንሆናለን ይላል አቤነዘር። ይህን ብዙም ያልተለመደ የአነዳድ ዘዴ በሰሞኑ ጉዞዋቸው ለሌሎች ለማስተዋወቅ መንገድ ከፍቶላቸዋል።
በዚህ ጉዞ ከአቤነዘር ሌላ 6 የስኬትቦርድ ነጂዎች አሉ። ሚካኤል ፋሲል ግን ዛሬ ምድቡ በቪዲዮና ፎቶ ማንሳት ስራ ላይ ነው። ሚካኤል በዚህ ጉዞው የቪዲዮ ዘገባውን ሲያሰናዳ እንደው የሰዉን አመለካከት እንዴት እንዳገኘው ገልፆልናል።
ከ500 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት በሰው ሀይል በሚንቀሳቀስ ስኬትቦርድ መንዳት መቼም ብዙ ጉልበት መጠየቁ አይቀሬ ነው። ትንሽ ብያደክምም መንገድ ላይ የምናያቸው ደስ የሚሉ ነገሮች ይበልጥ ቀጥለን እንድነዳ ያበረታቱናል ይላል አቤነዘር። ምባልባት ነገ አልያም እሁድ ተጓዦቹ እና አብሮዋቸው ያሉት አጃቢዎች ሀረር እንደሚደርሱ ተስፋ ያደርጋሉ።
እስካሁን ስለነበራቸው ጉዞ ማወቅ ከፈለጋችሁ የድምፅ ዘገባውን ይጫኑ።
ልደት አበበ
ተክሌ የኋላ