በስኬትቦርድ ከአዲስ አበባ እስከሐረር ጉዞ
ዓርብ፣ ሚያዝያ 18 2005ማስታወቂያ
ትንሽ ነው ከጠፍጣፋ እንጨት የተሰራ፣አራት ጎማዎች ያሉት ምናክባትም መካከለኛ መክተፊያ ያልላል። ሰሞኑን ፤አዲስ አበባን ከሀረር ከሚያገናኘው ጎዳና ላይ እንደዚህ አይነት እንጨት ላይ ቆመው ወይንም በአንድ እግራቸው እየገፉና ጣውላው ላይ ዘለው እየቆሙ የሚጓዙ ወጣቶች አይታችሁ ከሆነ ፤ የስኬትቦርድ ነጂዎች ናቸው። ስለዚህ ረዥም ጉዞ እና የስኬት ቦርድ አነዳድ የዛሬው የወጣቶች አለም ትኩረት ይሆናል።