በስህተት የተገደለው ኢትዮጵያዊ
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 19 2009ማስታወቂያ
ከዛሬ 27 ዓመት በፊት ለንደን ውስጥ የራሱን ህይወት አጥፍቷል የተባለ ኢትዮጵያዊ ጉዳይ ፍትህ እንዲያገኝ ቤተሰቦቹ እና ወዳጆቹ በድጋሚ ጠየቁ ። የሟች ወንድም እንደሚሉት ፣ፖሊስ ሞገስ አባይ የተባለው ወንድማቸው በጎርጎሮሳዊው ሰኔ 30 1990 ከሚኖርበት ህንፃ ራሱን ወርውሮ ህይወቱን አጥፍቷል ቢልም በወቅቱ የተገኙት መረጃዎች ግን አጠራጣሪ ነበሩ ። የአይን ምስክሮችም ሆኑ የሟች ወንድም ሞገስ ያኔ የራሱን ህይወት ማጥፋቱን የሚጠቁም ማስረጃ እንዳላዩ ነው የሚናገሩት ። በቅርቡ ደግሞ የሞገስ ስም በስህተት ከተገደሉ ሰዎች ስም ዝርዝር ውስጥ በመገኘቱ ወንድሙ እና ጓደኞቹ መንግሥት ፍትህ እንዲሰጣቸው እየጠየቁ ነው ። ዝርዝሩን የለንደንዋ ወኪላችን ሀና ደምሴ ልካልናለች ።
ሀና ደምሴ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ