በሰዉ እጅ የተገደለዉ ኤርትራዊ ጉዳይ
ዓርብ፣ ጥር 15 2007ማስታወቂያ
በብዙዎች የተገመተዉ በዉጭ ሀገር ዜጋ ላይ ጥላቻ ያሳያሉ የሚባሉት ወገኖች ከሀገሩ ከተሰደደ ብዙም ወራት ያልሆነዉን ኤርትራዊ ሕይወት ቀጥፈዉ ይሆናል የሚል ነበር። ይህም ነዉ ዘረኝነት የሚያሳዩ ወገኖቻቸዉን ተቃዉመዉ አደባባይ የወጡ ጀርመናዉያን ሳይቀሩ ፎቶዉን ይዘዉ ፍትህ እንዲያገኝ ድምፃቸዉን እንዲያሰሙ ያደረጋቸዉ። የፖሊስ ምርመራ ግን ያመላከተዉ ሌላ ነዉ። በምሥራቅ የጀርመን ግዛት ድሬዝደን ከተማ በሰዉ እጅ ሕይወቱ ስላለፈችዉ ወጣቱ ስደተኛ ካሊድ የአሟሟት ሁኔታ የተከታተለዉን ዘጋቢያችን ይልማ እንደሚከተለዉ አጠናቅሮ ልኮልናል።
ይልማ ኃይለሚካኤል
ሸዋዬ ለገሠ
ኂሩት መለሰ