በርሊን ማራቶን- አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ተሰበረ
እሑድ፣ መስከረም 18 2007ማስታወቂያ
የ30 ዓመቱ ኬንያዊ ለ41ኛ ጊዜ በጀርመን መዲና በተካሄደው የማራቶን ውድድር (2: 02: 57) በመሮጥ ከዓለም 2 ሰዓት ከ 03 ደቂቃ በታች ከሮጡ ሰዎች የመጀመሪያውም ሆኗል። ዴኒስ ኪሜቶ በሀገሩ ዜጋ ዊልሰን ኪፕሳንግ ተጠብቆ የነበረውን የዓለም ክብረ ወሰን በ26 ሰከንድ አሻሽሏል። በውድድሩ ኬንያዊው ኤማኑኤል ሙታይ 2ኛ፣ ኢትዮጵያዊው አበራ ኩማ (2: 05: 56) 3ኛ ሆነዋል። በውድድሩ ውጤት ያስመዘግባል በሚል በከፍተኛ ሁናቴ ሲጠበቅ የነበረው ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ፀጋዬ ከበደ ውድድሩን አቋርጦ ወጥቷል። በበርሊኑ የሴቶች የማራቶን ውድድር ደግሞ ኢትዮጵያዊቷ ትርፊ ፀጋዬ (2: 20: 18) ሰከንድ በመሮጥ አሸናፊ ሆናለች ። የሀገሯ ልጅ የሆነችው ፈይሴ ታደሰ 2ኛ ስትወጣ የዩናይትድ ስቴትሷ ሻለን ፍላንገን በ3ኛነት አጠናቃለች። በውድድሩ ኢትዮጵያውያቱ ታደለች በቀለ እና አበበች አፈወርቅ 4ኛ እና 5ኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቀዋል።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ልደት አበበ