በሞያሌ ኮሌራ ወይስ አጣዳፊ ተቅማጥ ?
ማክሰኞ፣ መጋቢት 8 2001ማስታወቂያ
ስለኮሌራው ወረረሽኝ ከዘገቡት አንዱ ኢሪን የተባለው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዜና አገልግሎት ሲሆን ዜና አገልግሎቱ የሞያሌ ሆስፒታል የጤና ባለሞያን ጠቅሶ እንደዘገበው በኮሌራ አስራ አራት ኢትዮጵያውያንና ኬንያውያን ሞተዋል ። ስለሞያሌው የኮሌራ ወረርሽኝ ዶይቼቬለ የአማርኛው ክፍል ያነጋገራቸው የኢትዮጵያ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባለስልጣን ግን በድንበር አካባቢ የተከሰተው ከፍተኛ ትኩሳት የታከለበት አጣዳፊ ተቅማጥና ተውከት እንጂ ኮሌራ ለመሆኑ ማረጋገጫ የለም ብለዋል ። ዝርዝሩን ታደሰ ዕንግዳው ከአዲስ አበባ ልኮልናል ።