በመጪው ዓመት ምርጫ ማካሄድ ይቻል ይሆን?
እሑድ፣ ግንቦት 25 2011ማስታወቂያ
በሌላ ወገን ደግሞ ምርጫ ለማካሄድ አስቀድሞ መሟላት የሚገባቸው መሠረታዊ ጉዳዮች መኖራቸውን በመዘርዘር ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለማካሄድ ተፈላጊውን ማከናወን ይቀድማል የሚሉ ወገኖች አሉ። የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ፣ የምርጫ አስፈጻሚ መዋቅሮች ዝግጅት፣ በየክልሉ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ያልተገደበ እንቅስቃሴ ማድረግ ፤ የሕግ እና የፍትህ ተቋማት ገለልተኛነት፣ በሀገሪቱ የሚታየው ያልሰከነ የመፈናቀል እና የፀጥታ ጉዳይን ቅድሚያ ሰጥቶ ደርዝ ማስያዝያ እንደሚገባ በማሳሰብም ፤ በዚህ ይዞታ ምርጫ አሁን ዋነኛው አሳሳቢ ጉዳይ እንዳልሆነም ያስረዳሉ። ከ100 የሚበልጡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ባሉባት ሀገር በቦርዱ በኩል እስካሁን አስፈላጊውን አሟልተው የተመዘገቡት 68 ፓርቲዎች መሆናቸውን ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ አስታውቋል። ዶይቼ ቬለ ለዚህ ሳምንት ኢትዮጵያ በመጪው ዓመት ምርጫ ማካሄድ አለባትን? ሲል ውይይት አካሂዷል። ሙሉውን ውይይት ከድምፅ ዘገባው ያድምጡ።
ሸዋዬ ለገሠ
ልደት አበበ