በላሊበላ ላይ የተደረገው ቅድመ ጥናት ተገመገመ
ሐሙስ፣ ግንቦት 8 2011ማስታወቂያ
በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት በተመዘገበው የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስትያናት ቅርስ ላይ ያንዣባበውን የአደጋ ስጋት ለመከላከል እና ቅርሱንም ለመጠገን የፈረንሳይ የቅርስ ጥናት ባለሙያዎች ቅድመ ጥናት አካሂደዋል። በፈረንሳይ መዲና ፓሪስ የዩኔስኮ ዋና መስሪያ ቤት ይህንኑ የምርመራ ውጤትን የገመገመ ውይይት ተደርጓል። ውይይቱ ለቀጣይ እርምጃዎችም አቅጣጫ ያስቀመጠ መሆኑ ተገልጿል።
የተለያዩ ባለሙያዎችን ከዩኔስኮ ዓለም አቀፍ ቅርስ ጥናት ጥበቃ ማዕከል፣ መንግስታዊው ያልሆነው የሀውልቶች እና ታሪክ ቦታዎች ድርጅት እንደዚሁም የፈረንሳይ እና የኢትዮጵያ ተወካዮችም በጋራ መድረኩ ላይ ተካፋይ ሆነውበታል። በውይይቱም ጥናቱን መሰረት በማድረግ በቅርሱ ላይ ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት የአካባቢውን ህብረተሰብ እና ቤተክርስቲያኒቱንም ባማከለ መልኩ ቅርሱን ለመታደግ የተግባር ስራ እንደሚደረግም ታውቋል።
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።
ሃይማኖት ጥሩነህ
ተስፋለም ወልደየስ
ኂሩት መለሰ