«ቅድሚያ ለሴቶች» የ 5 ኪሎ ሜትሩ ሩጫ
ዓርብ፣ መጋቢት 11 2007ትላልቅ የሩጫ ውድድሮች በአዲስ አበባ ከተማ መካሄድ ከጀመሩ ዓመታት ተቆጠሩ። ከነዚህ የሩጫ ውድድሮች መካከል ባለፈው እሁድ የተካሄደው «ቅድሚያ ለሴቶች» የ 5 ኪሎ ሜትር ሩጫ አንዱ ነው። ይህ ውድድር የተዘጋጀው በታላቁሩጫበኢትዮጵያኃላፊነቱየተወሰነየግልማህበርነው። ከታዋቂው እና ባለፈው ህዳር ለ 14ኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ከተካሄደው «ታላቁሩጫ» በተጨማሪ ሌላ፤ ሴቶች ብቻ የሚሳተፉበት ሩጫ ማዘጋጀት ለምን አስፈለገ? የዚህ ውድድር አዘጋጅ ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ኤርሚያስ አየለን ጠይቀናል።
በዚህ የሩጫ ውድድር ከተሳተፉት ሴቶች አንዷ፤ ባለፈው ዓመት ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በህግ የተመረቀችው ህሊና ብርሃኑ ናት። ህሊና፤ ሴቶች ብቻ በሚወዳደሩበት ሩጫ ስትሳተፍ ይህ 4ኛ ጊዜዋ ነው። ለወጣቷ ሩጫው ከስፖርት የበለጠ ትልቅ አላማ አለው፤ስለዚህ አላማ ወጣቷ ገልጻልናለች።
በዶይቸ ቬለ የፌስ ቡክ ገጽ ላይ ያለ ዕድሜ ጋብቻ በመፈፀም እና በተለያዩ ምክንያቶች ልጃ ገረዶች ወደ ትምህርት ቤት የማይላኩበት ሁኔታ ኢትዮጵያ ውስጥ ምን ያህል አሳሳቢ እንደሆነ ጠይቀን ነበር። ከደረሱን አስተያየቶች ጥቂቶቹ፤
ስለ የ«ቅድሚያ ለሴቶች» የ 5 ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድር እና አላማ የበለጠ ከወጣቶች ዓለም ዝግጅት የድምፅ ዘገባ ያገኛሉ። ከዚህ በታች ይጫኑ
ልደት አበበ
ተክሌ የኋላ