ቅሬታ በድሬዳዋ ማረሚያ ቤት ላይ
ረቡዕ፣ የካቲት 27 2011ማስታወቂያ
በድሬደዋ አስተዳደር በሚገኘው የፈደራል ማረሚያ ቤት ከተካሄደው የምርመራ ውጤት በኋላ 33 ያህል ታራሚዎች ወደ ሌላ ማረሚያ ቤት እንዲወሰዱ መደረጉ ቅሬታ አስነስቷል። ቅሬታ አቅራቢዎቹ ለDW እንደተናገሩት ታራሚዎቹ በግንባታ ላይ ወደሚገኝ እና ሥራ ወዳልጀመረ አዲስ ማረሚያ ቤት ተወስደዋል፤ ቤተሰብም ሊጠይቃቸው አልቻለም። የድሬዳዋው ወኪላችን መሳይ ተክሉ ስለ ቀረቡት ቅሬታዎች የማዕከሉን ሃላፊ ለማነጋገር ቢሞክርም ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸውን ዘግቧል።
መሳይ ተክሉ
ኂሩት መለሰ
ተስፋለም ወልደየስ