ቃለ ምልልስ ከደቡብ ሱዳን አምባሳደር ጋር
ረቡዕ፣ ግንቦት 10 2008ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን አምባሳደር ጀምስ ፒትያ ሞርገን የኢትዮጵያ እና የደቡብ ሱዳን ግንኙነት ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቁ ። የሹመት ደብዳቤያቸው በቅርቡ ያቀረቡት አዲሱ አምባሳደር ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ ከደቡብ ሱዳን ተሽግረው ጋምቤላ በገቡ ታጣቂዎች ከሳምንታት በፊት የተፈፀመውን ግድያ እገታ እና ዘረፋ አውግዘዋል ። አምባሳደሩ በዚሁ ጥቃት ታግተው ከተወሰዱት ህፃናት መካከል በሁለቱ ሃገራት የጋራ ጥረት የተወሰኑት ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውን ተናግረው የተቀሩትን ለማስመለስ ደግሞ አሰሳው መቀጠሉን አስታውቀዋል ። ያነጋገራቸው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝር ዘገባ አለው ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ