ቃለ ምልልስ ከአባ ሙሴ ጋር
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 9 2009ማስታወቂያ
ህገ ወጥ ስደተኛ አሻጋሪዎችን ይረዳሉ በሚል ተጠርጥረው የደቡብ ኢጣላያዋ የትራፓኒ ከተማ አቃቤ ህግ ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን የገለጸላቸው አባ ሙሴ ዘርአይ ከተባሉት ህገ ወጦችም ጋር ሆነ ከሌሎች በዚህ ሥራ ከተሰማሩ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት እንደሌላቸው ለዶቼቬለ አስታወቁ ። አበሻ ኤጀንስያ የተባለው መቀመጫውን ሮም ኢጣልያ ያደረገው ስደተኞችን የሚረዳው ግብረ ሰናይ ድርጅት ዋና ሃላፊ አባ ሙሴ ለሮሙ ወኪላችን ተክለ እዝጊ ገብረ እየሱስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳሉት ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑ ተገcጾላቸዋል እንጂ በድርጊቱ ተጠርጥረው ክስ አልቀረበባቸውም። ቃለ ምልልሱ ተክለእዝጊ ስለደረሳቸው ደብዳቤ ምን አስተያየት እንዳላቸው ላቀረበላቸው ጥያቄ አባ ሙሴ በሚሰጡት በሚሰጡት መልስ ይጀምራል.
ተክለ እዝጊ ገብረ እየሱስ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ