የፖለቲካው ትኩሳት ሁከት እንዳያስነሳ ተሰግቷል
ቅዳሜ፣ መስከረም 13 2010ማስታወቂያ
በራይላ ኦዲንጋ የሚመራው የተቃዋሚዎች ጥምረት የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ቢያወድስም ለጥቅምት 16 ቀን ከተቆረጠለት ድጋሚ ምርጫ በፊት በምርጫ አስፈጻሚው በኩል መስተካከል ይገባቸዋል ያላቸው ጉዳዮች ካልተደረጉ በምርጫው ላይሳተፍ እንደሚችል አስጠንቅቋል፡፡ በስልጣን ላይ ያሉት የፕሬዝዳንት አሁሩ ኬንያታ ቀንደኛ ተፎካካሪ ራይላ ኦዲንጋ ትላንት ከዶይቼ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስም ይህንኑ ማስጠንቀቂያ ደግመውታል፡፡ ሳምንታዊው “ትኩረት በአፍሪቃ” ዝግጅታችን አወዛጋቢውን የኬንያን ምርጫ ጉዳይ በዋናነት ይመለከታል፡፡ የቶጎ መንግስት ህገመንግስቱን ለማሻሻል በመሞከሩ የተቀሰቀሰበትን ተቃውሞም በአጭሩ ይቃኛል፡፡
ገበያው ንጉሴ
ተስፋለም ወልደየስ