ሻምበል ጉታ ዲንቃ በደቡብ አፍሪቃ6 ታኅሣሥ 2006እሑድ፣ ታኅሣሥ 6 2006ሻምበል ጉታ ዲንቃ በአፄ ኃይለስላሴ ዘመነ መንግስት ኔልሰን ማንዴላ ለትጥቅ ትግል ስልጠና አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በቆዩበት ወቅት ጠባቂያቸው ከነበሩ መኮንኖች መካከል አንዱ ናቸው። የማንዴላ የቀብር ስርዓት ላይ እንዲገኙ ለማድረግ በመላው ዓለም ያሉ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል። ይህ ጥረት ከምን ደረጃ ላይ ደረሰ?https://p.dw.com/p/1Aa5vምስል Reutersማስታወቂያ ስቱዲዮ ከመግባቴ ጥቂት ቀደም ብሎ ደቡብ አፍሪቃ በመደወል ሻምበሉን ለማስመጣት ተጀምሮ የነበረውን ጥረት ሲያስተባብሩ ከነበሩ ኢትዮጵያውያኖች መካከል አንዱ የሆነው አርቲስት በላይ አዳነን አነጋግሬዋለሁ። ሻምበል ጉታ ዲንቃም ስለደቡብ አፍሪቃ ቆይታቸው የሚነግሩን ይኖራል። ቃለመጠይቁን ከታች የሚገኘውን የድምፅ ማጫወቻ በመጫን ያድምጡ ማንተጋፍቶትስለሺ ልደትአበበ