የሸገር 102.1 ኤፍ ኤም
ረቡዕ፣ ጥቅምት 15 2010ማስታወቂያ
ሸገር 102.1 ኤፍ ኤም ራድዮ የተመሠረተበትን አሥረኛ ዓመት ትናንት በርካታ ታዳሚዎች በተገኙበት በሸራተን አዲስ አክብሯል። ለየት ባለ አቀራረቡ ተደማጭነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ የሚነገርለት የራድዮ ጣቢያው መሥራች እና ባለቤት ወይዘሮ መዓዛ ብሩ ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ የስኬታቸው ሚስጥር አማራጭ ሆነው መቅረብ መቻላቸው መሆኑን ገልፀዋል። ሸገር 102.1 ኤፍ ኤም ራድዮ ቀለል ባለ አቀራረብ እያዝናኑ በሚያስተምሩ ዝግጅቶቹ ይበልጥ ሳቢ መሆን መቻሉን አስተያየት ሰጭዎች ይናገራሉ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ