ሶርያ፤ የተኩስ አቁም ስምምነት
ቅዳሜ፣ የካቲት 19 2008ማስታወቂያ
ኾኖም መቀመጫውን ብሪታኒያ ያደረገው የሶርያ የሰብዓዊ መብት ታዛቢ ቡድን ራሱን «እስላማዊ መንግሥት» እያለ የሚጠራው ቡድን ብርቱ ውጊያ መክፈቱን ጠቅሷል። በውጊያው ቢያንስ 45 የ IS ተፋላሚዎች እና 20 የኩርድ ተዋጊዎች እንዲሁም የፀጥታ ኃይላት ዛሬ መገደላቸውንም ቡድኑ አክሎ ገልጿል።
ምንም እንኳን የሩሲያ የጦር አይሮፕላኖች ዓርብ ዕለት በሶርያ የመንግሥት ተቃዋሚ አማፂያን ላይ ጠንካራ የኃይል ርምጃ የወሰዱ የነበረ ቢሆንም ዛሬ አይሮፕላኖቹ በሰማይ ላይ አልተስተዋሉም። ዩናይትድ ስቴትስ እና ሩሲያ በሳምንቱ መጀመሪያ ነበር ለተኩስ አቁም የተስማሙት። ይህ ስምምነት በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሰው እና ራሱን እስላማዊ ቡድን ሲል የሚጠራውን የሽብር ቡድን እና የአል ኑርሳ ግንባር ቡድንን አያካትትም። ተኩስ አቁሙ ከጀመረ ጊዜ አንስቶ በጥቂት አካባቢዎች ብቻ የተኩስ ልውውጥ እና ውጊያ ተስተውሏል።
ልደት አበበ
ማንተጋፍቶት ስለሺ