ሶሪያውያን ስደተኞች በቱርክ
ሐሙስ፣ ሰኔ 2 2003ማስታወቂያ
በተለይ ቱርክ ድንበር አቅራቢያ በሚገኝ ከተማ ውስጥ 120 ያህል የመንግሥት ወታደሮች ከተገደሉ ወዲህ ወደ ቱርክ የሚሸሹት የሶሪያ ስደተኞች ቁጥር ጨምራል ። በወታደሮቹ ግድያ ምክንያት የሶሪያ ልዩ ኮማንዶ በከተማይቱ ላይ የተጠናከረ ጥቃት ሊሰነዝር ይችላል የሚል ስጋትም ሰፍኗል ። በአሁኑ ሰዓት በርካታ የሶሪያ ስደተኞች ወደ ቱርክ መጉረፋቸውም ቱርክ ስለ ሶሪያ መንግሥት ያላትን አቋም ሊያስቀይር ይችል ይሆናል የሚል ግምት አሳድሯል ። ኡልሪሽ ፒክ ከኢስታንቡል ለላከው ዘገባ ሂሩት መለሰ
ሂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ