ስደትን ለመግታት ያለመዉ የአዉሮጳ ኮሚሽን
ሐሙስ፣ ጥር 18 2009ማስታወቂያ
የአዉሮጳ ኅብረት ቀደም ሲል ስደተኞች ወደ አዉሮጳ እንዳይገቡ ለመቆጣጠር እና ለመመለስ የሚያስችሊ ስምምነቶችን ከቱርክ እና ከአፍሪቃ መሪዎች ጋር መፈራረሙ ይታወሳል። የአሁኑ ተጨማሪ ርምጃ በተለይ የቫሌታዉን ስምምነት ለማጠናከርና ይበልጥም ዉጤታማ ለማድረግ መሆኑን ትናንት በብራስልስ በጉዳዩ ላይ ጋዜጣዊ መግለቻ የሰጡት የኅብረቱ የዉጭ ጉዳይ ኃላፊ ፌደሪካ ሞጎረኒ እና የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽነር ዲሚትሪስ አብራምፖሎስ ማስታወቃቸዉን በስፍራዉ የተገኘዉ ዘጋቢያችን ገበያዉ ንጉሤ የላከዉ ዘገባ ያመለክታል።
ገበያዉ ንጉሤ
ሸዋዬ ለገሠ
አዜብ ታደሰ