ስደተኞች የሚሸጡት ለወሲብ ባርነትና ለጉልበት ሥራ ነው
ሰኞ፣ ሚያዝያ 9 2009ማስታወቂያ
ወደ አውሮፓ ለመሻገር፣ ሊቢያ የሚሄዱ አፍሪቃውያን ስደተኞች በሰው አሻጋሪዎች ለባርነት እንደሚሸጡ ዓለም ዓቀፉ የስደት ጉዳይ ድርጅት በምህጻሩ IOM አስታወቀ። ድርጅቱ ከባርነት ያመለጡ ስደተኞችን ዋቢ አድርጎ ባወጣው ዘገባ መሠረት አንድ ስደተኛ ከ200 እስከ 500 ዶላር ነው የሚሸጠው። በተሸጠበት ስፍራም በአማካይ ከሁለት እስከ ሦስት ወር እንዲቆይ ይደረጋል። ለዚህን መሰል ዘመናዊ ባርነት ከተዳረጉት መካከል የምዕራብ አፍሪቃ ሀገራት ዜጎች እንደሚገኙበት ድርጅቱ አስታውቋል። የዋሽንግተን ዲሲው ወኪላችን መክብብ ሸዋ ዝርዝር ዘገባ አለው ።
መክብብ ሸዋ
ኂሩት መለሰ