ስደተኞችን የሚያሰለጥነዉ ሪኮኔክት
ሐሙስ፣ ሰኔ 12 2006ማስታወቂያ
ሰዎች ከሀገራቸዉ ተሰደዉ በሚጠጉባቸዉ ሃገራት ለደህንነታቸዉ ሊሰጣቸዉ ከሚገባቸዉ ከለላ ሌላ በሄዱበት የተሻለ ኑሮ እንዲያገኙ የሚረዱ ተቋማት አሉ። ብሪታንያ ዉስጥ የሚንቀሳቀስ አንድ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ስደተኞች ጥገኝነት ባገኙባት ሀገር ራሳቸዉን አሻሽለዉ የበኩላቸዉን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ አስችሏል። በጎርጎሪዮሳዊዉ 2003ዓ,ም የተቋቋመዉ ሪኮኔክት የተሰኘዉ ይህ ድርጅት እስካሁን 50 ስደተኞችን ደረጃዉን በጠበቀ ሁኔታ በመምህርነት አሠልጥኗል ከእነዚህ ዉስጥም 13ቱ ኢትዮጵያዉያን እንደሆኑ የሎንዶን ዘጋቢያችን ድልነሳ ጌታነህ የላከልን ዘገባ ያስረዳል።
ድልነሳ ጌታነህ
ሸዋዬ ለገሠ
ሂሩት መለሰ