ስዊድን በጉዲፈቻ ያደጉ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን
ሰኞ፣ ሚያዝያ 6 2006ማስታወቂያ
በጉደፈቻ ስዊድን ተወስደው ያደጉ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያንና በሚያጋጥሟቸው ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ላይ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መከሩ ። ስዊድን በጉዲፈቻ ያደጉ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ማህበር ባለፈው እሁድ ስቶክሆልም ስዊድን ውስጥ ባዘጋጀው ስብሰባ የማህበሩ አባላትና ሃገር ቤት የሚገኙ ወላጆቻቸው እርዳታና ምክር በሚያገኙበት መንገድ እንዲሁም በጉዲፈቻ ማዕከል ምሥረታ ላይ ተነጋግረዋል ። በዚሁ ስብሰባ ላይ የተገኙት በስዊድን የኢትዮጵያ አምባሳደር የማህበሩን አባላት ችግሮች ለመፍታት ኢትዮጵያና ስዊድን የሚገኙ ጉዳዩ የሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች በትብብር መሥራት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል ። ስብሰባውን የተከታተለው የስቶክሆልሙ ዘጋቢያችን ቴዎድሮስ ምህረቱ ዘገባ አለው ።
ቴዎድሮስ ምህረቱ
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ