ስዊድን ስለ-ስደተኞች ጉዳይ ሕግን ማጥበቋ
ረቡዕ፣ ኅዳር 15 2008ማስታወቂያ
በስዊድን የሚገኘዉ የዶይቼ ቬለ ዘጋቢ ቢዮን ዳክ እንደተመለከተዉ ወደ ስዊድን ለሚገባም ሆነ እዚያ ለገቡ ስደተኞች የስዊድን መንግሥት የነበረዉን ሕግ ማጥበቁ እስከዛሬ ስለስዊድን የነበረዉን አመለካከት ሁሉ ቀይሮታል። በስዊድን መንግሥት የስደተኛ ጉዳይ የፖለቲካ ዉሳኔ በሀገሪቱ የሚገኙ ቀኝ አክራሪዎች መደሰታቸዉን ሳይደብቁ እፎይ በማለት መግለፃጫ መስጠታቸዉ ተመልክቶአል። ከስቶኮልም የዶይቼ ቬለዉ ተወካይ ቢዮን ደክ የስዊድን የስደተኛ ጉዳይን ሕግ ማጥበቅን በተመለከተ የዘገበዉን የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤል አቀናብሮ ልኮልናል።
ይልማ ኃይለሚካኤል
አዜብ ታደሰ