1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስዑዲ ነዋሪዎች አስተያየት

ረቡዕ፣ መጋቢት 26 2010

ዶክተር ዓብይ አህመድ በንግግራቸው ትኩረት የሰጧቸውን አበይት ተግባራት ለማከናወን አስተያየት ሰጪዎቹ እንዳሉት በገዢው ፓርቲ ኢህአዲግ  እና በመንግስት መካከል ይታያል ያሉትን መርህ አልባ ግንኙነት መልክ ማስያዝ ይገባቸዋል፡፡

https://p.dw.com/p/2vUco
Äthiopien Vereidigung Premierminister Abiy Ahmed
ምስል picture-alliance/AA/M. W. Hailu

የሪያድ ነዋሪዎች አስተያየት


የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ በበዓለ ሲመታቸው ንግግር ያነሷቸውን ጽንሰ ሐሳቦች ተግባራዊ ለማድረግ በፓርቲያቸው ኢህአዴግ ውስጥ ያለው ስር የሰደደ የጋራ አመራር ይፈቅድላቸዋል ብለው እንደማያምኑ በሪያድ ሳዑዲ ዓረቢያ የሚኖሩ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን  አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ ዶክተር አብይ አህመድ በንግግራቸው ትኩረት የሰጧቸውን አበይት ተግባራት ለማከናወን አስተያየት ሰጪዎቹ እንዳሉት በገዢው ፓርቲ ኢህአዲግ  እና በመንግስት መካከል ይታያል ያሉትን መርህ አልባ ግንኙነት መልክ ማስያዝ ይገባቸዋል፡፡ ዝርዝሩን ስለሺ ሽብሩ ከሪያድ ልኮልናል። 
ስለሺ ሽብሩ 
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ