ሳክሲፎኒስት ጌታቸዉ መኩሪያ አረፈ
ማክሰኞ፣ መጋቢት 27 2008ማስታወቂያ
«የሳክሲፎኑ ንጉስ» በመባል የሚታወቀዉ አንጋፋ ሙዚቀኛ ጌታቸዉ መኩሪያ አረፈ።ዛሬ ተቀበረ።80 ዓመቱ ነበር።ጌታቸዉ ከ1940ዎቹ መጀመሪያ ጀምሮ መጀመሪያ ዋሽንትን በመሳሰሉ ባሕላዊ ሙዚቃዎች ኋላ ደግሞ ለረጅም ጊዜ በታወቀበት ሳክሲፎን የሙዚቃ መሳሪያን በመጫዎት ልዩ ችሎታዉን ያሥመሠከረ ታላቅ የሙዚቃ ሰዉ ነበር።ጌታቸዉ መኩሪያ ባለትዳርና የ11 ልጆች አባት ነበር።ሥለ ጌታቸዉ ሥራና ችሎታ የሙዚቃ ቀማሪ ዶክተር ሙላቱ አስታጥቄን እና ደራሲ አያልነሕ ሙላቱን በስልክ አነጋግሬያቸዋለሁ።
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ