ቁጥሩ የማይታወቅ ሰዉ ሞተ
ዓርብ፣ ሐምሌ 12 2011ማስታወቂያ
የሲዳማ ዞን በክልል እንዲደራጅ የቀረበዉ ጥያቄ አፋጣኝ አወንታዊ መልስ እንዲሰጠዉ ግፊት የሚያደርጉ የሲዳማ ፖለቲከኞች በተለይ ወጣቶች በየከተማዉ ከሰፈረዉ የፀጥታ አስከባሪ ጋር እየተጋጩ ነዉ። ነዋሪዎች እንደገለፁት በግጭትና ሁከቱ ቁጥራቸዉ በዉል ያልታወቁ ሰዎች ተገድለዋል።መኪኖች፤ መኖሪያና መስሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል። መደብሮች ተመዝብረዋልም። የተለያዩ ከተሞችን የሚያገናኙ የመኪና መንገዶች ሲዘጉ፤ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት በከፊል ተቋርጧል። ሐዋሳ ዉስጥ ትናንት በፀጥታ አስከባሪዎችና በወጣቶች መካከል በተፈጠረዉ ግጭት ቢያንስ አንድ ሰዉ ተገድሎ፣ ሌሎች ሦስት ቆስለዋል። ወኪላችን ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ እንደዘገበዉ ሐዋሳ ዛሬ ተረጋግታለች።
ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ