1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የድንበር ማካለል ጉዳይ እንዲፋጠን ጠየቀች

Merga Yonas Bula
ዓርብ፣ ሚያዝያ 26 2010

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አሕመድ ትናንት ሱዳንን በጎበኙበት  ጊዜ የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር የሱዳን እና  የኢትዮጵያን አለመግባባት ለማስወገድ የሁለቱ ሐገራት ድንበር ባስቸኳይ እንዲካለል ዘይቀዋል።

https://p.dw.com/p/2xC0y
Infografik Karte Grand Ethiopian Renaissance Dam ENG

Ethio-Sudan border demarcation - MP3-Stereo

በስብሰባው ወቅት የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ከፀጥታ አካላት የተወጣጣ የድንበር ኮሚቴ የመመሥረትን አስፈላጊነት ተናግረዉ፤ ኮሚቴዉም በድንበር አከባብ ያለዉን የፀጥታ ችግሮችን እንድያጣና፤ የሁለቱን ሀገሮች የጋራ ድንበር ጠባቂ ሃይል እንድቋቋምና የድንበር ከለላዉን እንድፋጠን ያደርጋል ማለታቸዉ ዘገባዎች አክሎበታል። ፕሬዚዳንት ባሽርም በካርታዎች እና በማመላከቻዎች ላይ ሁለቱም አገራት ምንም ልዩነት እንደሌላቸዉም ጠቅሰዋል።

በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል ያለዉ የድንበር ማከለላ ጥያቄ ለዓመታት የዘለቀ እንደሆነ የገለጹት በጀርመን የሱዳን ኤምባስ አምባሳደር በደር ኤልዳኢን አብዳላ ሁለቱም አገራት በካርታ ላይ ያለዉ የድንበር መሰመር ላይ መሰማማታቸዉን ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል።

አምባሳደር በደር ኤልዳኢን አብዳላ:«በካርታዉ ላይ የሉም ነገር በጣም ግልፅና ሁሉም የተስማሙበት ጉዳይ ነዉ። ስለዝህ ቀሪዉ መሬት ላይ ድንበሩን ማካለል ነዉ። ይሄ ደግሞ እስካሁን አልተጀመረም። ይህንን ነዉ ክቡር ፕሬዚዳንት ባሽር  በሁለቱም አገሮች መካካል ያለዉን ድንበር የማካለል ስራ መጀመር እንዳለበት ትናንት የጠየቁት።»

ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር ባነሱት የድንበር ማካለል ጥያቄም ሆነ በዚሁ ጉዳይ ላይ የሱዳን መገናኛ ብዙሃን ይዘዉ በወጡት ዘገባ ላይ በኢትዮጵያ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም ለዶይቸ ቤለ አስተያየት መስጠት አልፈለጉም።

በደቡብ ምስራቃዊ ሱዳን በገዳሬፍ ግዛት አል-ፋሻጋ በተባለ ቦታ በኢትዮጵያና በሱዳን ድንበር አካባብ ያሉት ገበሬዎች በመሬት ይገባኛል ጥያቄ እንደሚጋጩ የዜና ምንጮች በተለያየ ጊዜ ያወጧቸው ዘገባዎች ያመለክታሉ።  በጀርመን የሱዳን ኤምባስ አምባሳደር በደር ኤልዳኢን አብዳላ፣ በዚህ ረገድ ምንም ግጭት የለም ይላሉ።

Äthiopien Meles Alem Sprecher Außenministerium
ምስል DW/G. Tedla

አምባሳደር በደር ኤልዳኢን አብዳላ: «ግን በሁለቱም በኩል ያሉት ገበሬዎች፤ በተለይም በኢትዮጵያ በኩል ያሉት ገበሬዎች ወደ ሱዳን ድንበር ተሻግሮ በመግባት መሬት ስያርሱ ነበር። ይሄ ደግሞ በሁለቱም መካከል ከግዜ ወደ ጊዜ ግጭት እንድፈጠር አድረገዋል። ግን ሁለቱም አገር መካከል ያለዉ መንፈስ የትብብር መንፈስ ነዉ። ስለዝህ በተለያዩ ደረጃዎች ትብብር አለ፤ ከፕሬስዳንቱ ጀምሮ እስከታች ድረስ በዝህ ጉዳይ ላይ ኮሚቴ ተቋቁመዋል። ስለዝህ በሁለቱም መንግስታት በኩል ምንም አሳሳቢ አለመግባባት የለም፤ ግን የነበረዉ ግጭት የኢትዮጵያ አርሶ-አደሮች የሱዳንን ድንበር ጥሰው ሲገቡ ብቻ ነበር።»

በዉይይቱም ወቅት ጠ/ሚ ዶክተር አብይ የሁለቱም የጋራ ጥቅም ለማስጠበቅ በድንበር አከባብ አሉ የሚባሉ ችግሮችን ለማስወገድ እንደሚሰሩና ሁለቱም ሀገራት ሊያሸንፏቸው የሚገቡ ትልቅ ፈተናዎች እንደሚጠብቋቸው መጥቀሳቸዉን ዘገባዎች አመልክተዋል።

አል-ፋሽጋ ወደ 250 ካሬሜትር እንደምሸፍንና ወደ 242, 8116 ሄክታር  ለግብርና የሚዉል መሬት እንዳለው ዘገባዎች ያመለክታሉ። በአከባቢዉም አትባራ፤ ሴታእትና ባስላም የተሰኙ ወንዞች እንደምገኙም ተጠቅሰዋል።

መርጋ ዮናስ

አርያም ተክሌ