ሱዳን በእሥራኤል ላይ የሰነዘረችው ወቀሳ
ሐሙስ፣ ጥቅምት 15 2005የሱዳን መንግሥት ለሰነዘረው ወቀሳ እሥራኤል አስተያየት ከመስጠት ተቆጥባለች። ይሁንና አንድ የእስራኤል ከፍተኛ ወታደራዊ ባለሥልጣን ዛሬ ሱዳንን አደገኛና አሸባሪ ሲሉ ወንጅለዋል ።የእሥራኤል መገናኛ ብዙኃን በሱዳን የያርሙክ ጦር መሣሪያ ፋብሪካ ላይ ስለተጣለው ጥቃትና ለጥቃቱ ሱዳን እሥራኤልን ተጠያቂ ስላደረገችበት ወቀሳ ምን ይላሉ?
በእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር የፖሊሲና የፖለቲካ ና ወታደራዊ ጉዳዮች ሃላፊ አሞስ ጊላድ እስራኤል ጥቃቱን መፈፀም አለመፈፀሟን ተጠይቀው በቀጥታ መለስ ከመስጠት ቶቅጥበዋል ። አሞስ ዛሬ ለእስራኤል ሬድዮ በሰጡት ቃለ ምልልስ ሱዳንን አደገኛ ና አሸባሪ ብለዋል ። አሞስ የሱዳን መንግሥት በኢራን ይደገፋል ከማለታቸውም በላይ የኢራን የጦር መሳሪዎች በበግብፅ ግዛት አድርገው ለሃማስና ለ ለሙስሊም አሸባሪዎች መሸጋጋሪያ መንገድም እያገለገለ ነው ሲሉም ከሰዋል ። የሱዳን ካቢኔ ትናንት ማምሻውን በጉዳዩ ላይ ስብሰባ ቢያካሂድም መግለጫ አላወጣም ። በጥቃቱ ማግስት ትናንት የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር አል በሽር የተገኙበት ፀረ እስራኤል ሰልፍ ተካሂዷል ። ወደ 300 የሚሆኑ ሰልፈኞች አሜሪካን በማውገዝ እስራኤልም ከምድር ገፅ እንድትጠፋ ጥሬ አቅርበዋል ። ሱዳን ትናንት እንዳስታወቀችው እስራኤልን በማንኛውም መልኩ መበቀሏ አይቀርም የሱዳን ማስታወቂያ ሚኒስትር አህመድ ቢላል ኦስማን
« አፀፋውን መመለስ አለብን ፤ ምክንያቱም በጣም በዝቷል ። ይህን ሲያደርጉ አሁን አራተኛ ጊዜያቸው ነው ። እኛም በየትኛውም ቦታ የሚገኙ የእስራኤልን ጥቅሞች የማጥቃት መብት አለን ። በርግጥ እስራኤልን አናጠቃም ። ሆኖም ማጥቃት የምንችልበት መንገድ አለን ። መልሱን የምንሰጥበት መንገድ አለን ። የኛን ሰዎች ገድለዋል ። እንዚህ ነፍሶች ርካሽ አይደሉም ። እናም እንዴት አፀፋውን እንደምንመልስ እናውቃለን ።»
ሚኒስትሩ አክክለው እንዳሉት የተደበደበው ፋብሪካ ባህላዊ የጦር መሣሪያዎችን የሚያመርት ነው ።
ግርማው አሻግሬ
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ
ሸዋዬ ለገሰ