ራድዮ ኤሬና8 መጋቢት 2002ረቡዕ፣ መጋቢት 8 2002በስደት ላይ ባሉ የኤርትራ ጋዜጠኞች አነሳሽነት የተቋቋመው ራድዮ ኤሬና የተሰኘው የሬድዮ ፕሬግራም ካለፈው ሀምሌ ወር ጀምሮ በየቀኑ በትግሪኛ ቋንቋ ወደ ኤርትራና አካባቢው ልዩ ልዩ ዝግጅቶችን በማስተላለፍ ላይ ነው ።https://p.dw.com/p/MVHCምስል DWማስታወቂያለአንድ ሰዓት ያህል የሚሰራጨው ይህ በሳተላይት አማካይነት የሚተላለፈው የራድዮ ፕሮግራም መቀመጫውን ፓሪስ ባደረገው በድንበር የለሹ የጋዜጠኞች ማህበር በዋናነትየሚረዳ ሲሆን ሌሎች የፈረንሳይ መገናኛ ብዙሀንና አንዳንድ ድርጅቶችም ለራድዮ ጣቢያው እገዛ ያደርጋሉ ። ገበያው ንጉሴ ከብራሰልስ ስለዚሁ የራድዮ ፕሮግራም ዘገባ ለኮልናል ። ገበያው ንጉሴ፤ ሂሩት መለሰ ሸዋዬ ለገሠ