ራይላ ኦዲንጋ የኬንያ ተቃዋሚዎች እጩ ሆነው ቀረቡ
ዓርብ፣ ሚያዝያ 20 2009ማስታወቂያ
የ72 አመቱ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒሥትር ራይላ ኦዲንጋ ብሔራዊ ላዕላይ ትብብር (National Super Alliance) የተባለው ጥምረት ይፋ እጩ ናቸው። ራይላ ኦዲንጋ ለኬንያ የፕሬዝዳንትነት መንበረ ሥልጣን ሲገዳደሩ ሁለተኛቸው መሆኑ ነው።ኦዲንጋ በእጩነት መቅረባቸውን ካረጋገጡ በኋላ «ኬንያውያንን ከግብፅ ወደ እስራኤል አሻግራችኋለሁ» ሲሉ ቃል ገብተዋል። ተቃዋሚዎቹ ኦዲንጋን በእጩነት ሲመርጡ ትርጉም ያለው ለውጥ ለማምጣት የግል ፍላጎቶቻቸውን መስዋዕት ማድረጋቸውን ተናግረዋል። ኬንያ ከዚህ ቀደም ባካሔደችው ምርጫ ደም አፋሳሽ ግጭት አስተናግዳለች።
ፍቅረማርያም መኮንን
እሸቴ በቀለ
ነጋሽ መሐመድ