ረሐብና የነጊልዶርፍ ዳግም ዘመቻ
ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 2 2004ማስታወቂያ
እንደ ሙዚቃ-ዳንኪራቸዉ ሁሉ ኢትዮጵያን ለመሳሰሉ በተደጋጋሚ በረሐብ ለሚጠቁ ሐገራት ርዳታ በማሰባሰብ፥ በጎ ምግባራቸዉም ሥም-ዝና ያተረፉት የአየርላንድ ተወላጆቹ ድምፃዉያን ቦኖ እና ቦብ ጊልዶፍ በረሐብና በምግብ እጥረት ለተጎዳዉ ሕዝብ የሚሰጠዉ የምግብ ርዳታ እንዲቀጥል አዲስ ዘመቻ እንደሚጀምሩ አስታወቁ።ድምፃዉያኑ እንደሚሉት «ONE-አንድ» የሚል ሥም የሰጡት ዘመቻቸዉ የሚያተኩረዉ የቡድን ሃያ-አባል ሐገራትን ድጋፍ በማግኘቱ ላይ ነዉ።ሁለቱ ድምፃዉያን ከተባባሪዎቻቸዉ ጋር ሆነዉ ዘመቻዉን በቅርቡ አዉሮጳና ሰሜን አሜሪካ ዉስጥ እንደሚጀምሩ አክለዉ ገልፀዋል።ጌታቸዉ ተድላ ሐይለጊዮርጊስ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።
ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ተክሌ የኋላ