1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሥራ ያቆሙት የአሊያንስ የከተማ አውቶቡሶች

ማክሰኞ፣ የካቲት 5 2011

በአዲስ አበባ እና ዙሪያዋ በ125 አውቶቡሶች የትራንስፖርት አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው አሊያንስ የብዙኃን ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት  ካለፉት ሦስት ወራት አንስቶ ከስምሪት ውጪ መኾኑን ዐስታወቀ።

https://p.dw.com/p/3DEgs
Blick aus meinem Fenster Addis Abeba Äthiopien
ምስል Solomon Mengist

አውቶቡሶቹ ጎማቸው ተንፍሶና አቧራ ለብሰው ቆመዋል

በአዲስ አበባ እና ዙሪያዋ በ125 አውቶቡሶች የትራንስፖርት አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው አሊያንስ የብዙኃን ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት  ካለፉት ሦስት ወራት አንስቶ ከስምሪት ውጪ መኾኑን ዐስታወቀ። ድርጅቱ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለበትን እዳ መክፈል ባለመቻሉ ከጥቅምት 28 ቀን 2011 ዓም ጀምሮ ተሸከርካሪዎቹ ሙሉ በሙሉ ከአገልግሎት እና መደበኛ ስምሪት ውጭ መሆናቸውን ለDW ተናግሯል፡፡ ድርጅቱ አሁን ላይ ምን ያህል እዳ እንዳለበት ቢጠየቅም መልሱን ከመናገር ተቆጥቧል፡፡ የአዲስ አበባው ወኪላችን ሰለሞን ሙጬ ተሸከርካሪዎቹ ከቆሙበት አካባቢ አንዱ በሆነው የካ አባዶ ተገኝቶ ባደረገው ቅኝት አውቶቡሶቹ ጎማቸው ተንፍሶ እና አቧራ ለብሰው መቆማቸውን አረጋግጧል፡፡  DW ተሸከርካሪዎቹ ከቆሙበት አካባቢ አንዱ በሆነው የካ አባዶ ተገኝቶ ባደረገው ቅኝት አውቶቡሶቹ ጎማቸው ተንፍሶ እና አቧራ ለብሰው መቆማቸውን አረጋግጧል፡፡ ዝርዝር ዘገባውን ልኮልናል።

ሰለሞን ሙጬ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ነጋሽ መሐመድ