ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ
ሰኞ፣ ታኅሣሥ 6 2001ማስታወቂያ
በዛሬው የስፖር ዝግጅታችን፤ በአውሮጳ ምድር የተከናወኑ አበይት የእግር ኳስ ውድድሮች፣ አትሌቲክስና እዚህ ጀርመን ውስጥ በጉጉት ሲጠበቅ ቆይቶ ቅዳሜ ማታ የተደረገ ያለም ከባድ ሚዛን የቡጢ ፍልሚያ ሰፊ ቦታ ተሰጥቷቸው ይተነተናሉ። ዝነኛው የዓለም ከባድ ሚዛን ቡጢኛ ዩክሬናዊው ቭላድሚር ክሊችኮ ቅዳሜ ማታ አሜሪካዊው ሀሲም ራህማንን አብረከረከ። ክሊችኮ በግራ እጁ ደጋግሞ የሰነዘራቸውን ከባድ ቡጢዎች መቓቓም የተሳነው ራህማን በስድስተኛው ዙር ተዘርሮም ነበር። ዳኛው ጠጋ ብለው ሲጠይቁት ጨዋታውን መቀጠል መፈለጉን የገለፀው አሜሪካዊ ቡጢኛ ከቀጣዩ ሰባተኛ ዙር በላይ ግን መዝለቅ አልቻለም።