የሞያሌን ግድያ በመቃወም ሰልፍ በለንደን ከተማ
ዓርብ፣ መጋቢት 7 2010ማስታወቂያ
ባለፈው ሣምንት ቅዳሜ በቦረና ዞን ሞያሌ ከተማ የመከላከያ ሠራዊት በነዋሪዎች ላይ የፈጸመው ግድያ በየአቅጣጫው ቁጣን ቀስቅሷል። የኮማንድ ፖስቱ ድርጊቱ በተሳሳተ መረጃ ምክንያት የተከሰተ መሆኑን ቢገልፅም የመከላከያ ኃይሉ ጥቃት ሆን ተብሎ የተፈጸመ የወንጀል ድርጊት እንደኾነ የገለጡ አሉ። የ10 ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው፣ ጥቂት በማይባሉት ላይም የአካል ጉዳት ያደረሰው እና በሺህዎች የሚቆጠሩትን ለስደት የዳረገውን የመከላከያ ሠራዊቱን ርምጃ በመቃወም ለንደን ከተማ ውስጥ ዛሬ ሰልፍ ተካሂዷል። የለንደኑን ተቃውሞ ሰልፍ የተከታተለዉን ዘጋቢያችን ድልነሳው ጌታነህን ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት ስለሰልፉ በስልክ አነጋግሬው ነበር። ድልነሳው የሰልፉን ዓላማ በማብራራት ይንደረደራል።
ድልነሳው ጌታነህን
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሠ