ምርጫ 2002 የመጨረሻዉ ምዕራፍ
ሐሙስ፣ ግንቦት 19 2002በኢትዮጽያ በመጭዉ እሁድ የሚካሄደዉ 4ኛዉ አገር አቀፍ ምርጫ በመጨረሻዉ ሰአትም ዉዝግቦች አልተለለዩም። የሲዳማ አርነት ንቅናቄ፦ «በደቡብ ክልል በአሮሪሳ ወረዳ የድምጽ መስጪያ ወረቀት በገዝዉ ፓርቲ አማካኝነት በሚስጢር እየታደለ ነዉ» ይላል፣ የመላዉ ኢትዮጽያ አንድነት ፓርቲም ተመሳሳይ ክስ ያቀርባል። የደቡብ ክልል ፕሪዝደንት አቶ ሽፈራዉ ሽጉጤ በሚወዳደሩበት የአሮሪሳ ወረዳ ተከሰተ የተባለዉን የድምጽ መስጪያ ወረቀት በሚስጥር መበተንን በተመለከተ የክልሉ ምርጫ ቦርድ እያጣራ መሆኑን ገልጾአል። መሳይ መኮንን ሠወስቱን ወገኖች አንጋግሯቸዋል።
ወደ ሰሜን ምዕራብ ኢትዮጽያ ስናቀና ደግሞ ወደ ባህር ዳር የተጓዘዉ ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ የምርጫዉ ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጾአል። ይሁን እና እዝያም ቢሆን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ቅሪታ ማሰማታቸዉ አልቀረም። ታደሰ እንግዳዉን ነጋሽ መሃመድ ስልክ ደዉሎ አግኝቶታል።
ተቃዋሚ ፓርቲዎች ገዥዉን ፓርቲ ኢሃኤግን ከመዉቀሳቸዉ ጋር አለማቀፉ ማህበረሰብ ኢትዮጽያ ዉስጥ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት ብዙም አልጣረም በማለት ቅሪታቸዉን እያሰሙ ነዉ። 8 የፖለቲካ ፓርቲዎችን የሚያጣምረዉ የኢትዮጽያ ፊደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ሊቀመንበር ፕሮፊሰር በየነ ጴጥሮስ ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ይህንኑ ቅሪታቸዉን በግልጽ አስታዉቀዋል። ፕሮፊሰር በየነ ጴጥሮስ የኢትዮጽያ መንግት መድረክን ግጭት ለመጫር እየተንቀሳቀሰ ነዉ ያለዉን ክስም አጣጥለዉታል። ሉድገር ሻዶምስኪ ከአዲስ አበባ የላከዉን የፕሮፊሰሩን መግለጫ መሳይ መኮንን አዘጋጅቶታል።
ምሥራቅ ኢትዮጵያም የምርጫዉ ዝግጅት ተጠናቅቆ-መራጭና ተወዳዳሪዎች የድምፅ መስጪያዉን ዕለት እየተጠባበቁ ነዉ።የድሬዳዋዉ ወኪላችን ዩሐንስ ገብረ እግዚ አብሄር እንደተከታተለዉ የአዉሮጳ ሕብረት የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን መሪ ቲስ ቤርማን ዛሬ ድሬዳዋ ዉስጥ የሚወዳደሩ ዕጩዎችን ፦ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችንና የምርጫ ቦርድ ተጠሪዎችን አነጋግረዋል።ነጋሽ መሐመድ ዩሐንስ ገ/እግዚአብሔርን በስልክ አነጋግሮታል።
መሳይ መኮንን
ታደሰ እንግዳዉ
ዩሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ