ምርጫ 2002እና ዝግጅቱ7 ሚያዝያ 2001ረቡዕ፣ ሚያዝያ 7 2001በቀጣዩ 2002ዓ,ም የሚካሄደዉ ምርጫ ግልፅ፤ ተዓማኒ፤ ፍትሃዊና ሰላማዊ እንደሚሆን ገዢዉ ፓርቲ ኢህአዴግ ከወዲሁ እየተናገረ ነዉ።https://p.dw.com/p/HXk3ከ1997ቱ ምርጫ ድምፅ ሰጪዎች አንዷምስል APማስታወቂያምርጫዉን የተሳካ ለማድረግም ስልታዊ ሰነድ ተዘጋጅቶ በገዢዉ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባላት መካከል ለዉይይት መበተኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታዉቀዋል። ምንም እንኳን መንግስት ይህን ቢልም ከ1997ዓ,ም ምርጫ የማይረሳ ተሞክሮ ቀስመናል የሚሉት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ኢህአዴግ የሚገልጸዉና በተግባር የሚያደርገዉ አይገናኝም ሲሉ ትችት እየሰነዘሩ ነዉ።